የቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ በተከሉበት ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የመታሰቢያ ፓርክ ሊሰራላቸው ነው፡፡
በመታሰቢያ ፓርኩ ውስጥ የጀኔራሉን ክብር በሚመጥን መልኩ የማስታወሻ ሀውልት እንደሚሰራላቸው የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
ችግኙን ከተከሉበት ከቦሌ ሩዋንዳ ጀምሮ እስከ አትላስ ሆቴል ያለው ጎዳና በስማቸው እንዲሰየም የከተማ አስተዳደሩ ወስኗል፡፡
በከተማው የሚገኙ የስነ-ህንጻና የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ባለሙያዎችም የጄኔራል ሰዓረን የማስታወሻ ሀውልት ንድፍ ሰርተው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል፡፡