15 Jul
15Jul

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደህንነት አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ  ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት እጩ ሆኑ።

 አቶ ዮሃንስ ቧያለው የአዴፓ ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው ተመርጠዋል።

 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሲያካሂድ የነበረውን የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል።

 ውይይቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የማዕከላዊ ኮሚቴው አቶ ዮሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ መምረጡን አስታውቋል።

በተመሳሳይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አገኘው ተሻገር የአዴፓ ስራ አስፈፃሚና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች አባል ሆነው ተመርጠዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዕጩ ርዕሰ መስተዳድርነት ቀርበዋል።

 የርዕሰ መስተዳደር ሹመቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።

 አቶ ተመስገን በአማራ ክልልና በፌዴራል የተለያዩ ተቋማት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሰርተዋል።

ለአብነትም የአገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር፣ የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና በሌሎች የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።

Comments
* The email will not be published on the website.
I BUILT MY SITE FOR FREE USING