15 Jul
15Jul

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከሰላም ኖቤል ተሸላሚዋ ማላላ ዩሱፍዛይ ጋር ተወያዩ።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በውይይታቸው ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ መማር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ መምክራቸው ተገልጿል፡፡ 

መንግስት ያለውን የትምህርት ፖሊሲ ለማሻሻል የትምህርት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን ገልፀው ማገዝ ለሚፈልግ ማንኛውም አካል አስፈላጊ ሁኔታዎችን እንደሚያመቹ ተናግረዋል፡፡

የሠላም የኖቤል ተሸላሚና የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት የሠላም መልዕክተኛ ማላላ ዩሱፍዛይ በስሟ የሚጠራው ፋውንዴሽን ለሴት ተማሪዎች ትኩረት ሠጥቶ በዓለም ደረጃ እየተንቀሳቀሰ የተለያዩ ድጋፎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግራለች፡፡ 

በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ተግባራትን በማከናወን ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ማገዝ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

Comments
* The email will not be published on the website.
I BUILT MY SITE FOR FREE USING