03 Jul
03Jul

በሊቢያ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በተፈጸመ የአየር ጥቃት 40 ሰዎች ሞቱ።

80 ሰዎች መጎዳታቸውንም የአገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ከሟቾቹ አብዛኛዎቹ አፍሪካዊያን ስደተኞች መሆናቸው ተገልጿል።

በመንግስታቱ ድርጅት የሚደገፈውና በጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሴራ የሚመራው አስተዳደር፥ ራሱን የሊቢያ ብሄራዊ ጦር እያለ የሚጠራውን ቡድን ኮንኗል።

በከሊፋ ሃፍታር የሚመራው የሊቢያ ብሄራዊ ጦር በበኩሉ በተፈጸመው ጥቃት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አለመመታቱን ገልጿል።

ይሁንና ከዚህ በኋላ በመዲናዋ ትሪፖሊ ከባድ ጥቃት እንደሚሰነዝር አስታውቋል።

Comments
* The email will not be published on the website.
I BUILT MY SITE FOR FREE USING